← ወደ ጡሩምባ ይመለሱ

የግላዊነት ፖሊሲ

ለመጨረሻ ጊዜ የተሻሻለው: ኅዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም. (19 November 2026)

ጡሩምባ (Turumba) ከባንክዎ ወይም ከሞባይል ዋሌትዎ በመልዕክት የሚደርስዎትን ክፍያ ጮክ ብሎ የሚነግርዎ የAndroid መተግበሪያ ነው። ያበለጸገውና የሚያስተዳድረው Buna Technologies PLC ነው። ይህ ፖሊሲ መተግበሪያው ምን እንደሚያነብ፣ ምን እንደሚያስቀምጥና ፈጽሞ የማያደርገውን ያብራራል።

በአጭሩ

  • ጡሩምባ ሙሉ በሙሉ በስልክዎ ላይ ይሰራል። አካውንትም ሰርቨርም የለውም።
  • የሚሰራው ካበሯቸው ባንኮችና ዋሌቶች በሚመጡ የክፍያ መልዕክቶች ላይ ብቻ ነው።
  • የሚያነበውም ሆነ የሚያስቀምጠው ምንም ነገር ወደ የትም አይላክም፤ የአጠቃቀም መከታተያ፣ ማስታወቂያ ወይም የብልሽት ሪፖርት የለም።

መተግበሪያው የሚያነበው

መልዕክት እንዲያነብ ከፈቀዱ ጡሩምባ እያንዳንዱን የሚገባ መልዕክት ማን እንደላከው ያያል። የሚሰራው በመተግበሪያው ውስጥ ካበሯቸው ባንኮችና ዋሌቶች በሚመጡ መልዕክቶች ላይ ብቻ ነው። ከሌላ ማንም የሚመጡ መልዕክቶች ችላ ይባላሉ፤ ፈጽሞ አይቀመጡም።

በምትኩ የማሳወቂያ መዳረሻን ከመረጡ ጡሩምባ የእነዚያን ባንኮችና ዋሌቶች መተግበሪያዎች እንዲሁም የመልዕክት መተግበሪያዎን ማሳወቂያዎች ያያል፤ የሚያስቀምጠው ከመረጧቸው ባንኮችና ዋሌቶች የመጡ የክፍያ መልዕክቶችን ብቻ ነው።

«ብር ገብቷል» የሚል መልዕክት ከባንክ ሳይሆን ከመደበኛ ስልክ ቁጥር ሲመጣ ጡሩምባ ያስጠነቅቅዎታል። ይህ ማጣራት የሚካሄደው በስልክዎ ላይ ነው።

መተግበሪያው በስልክዎ ላይ የሚያስቀምጠው

ታሪክዎንና የዕለት ገቢዎን ለማሳየት ጡሩምባ ለሚሰራበት እያንዳንዱ የክፍያ መልዕክት የሚከተሉትን በስልክዎ ላይ በመተግበሪያው የግል ማከማቻ ውስጥ ያስቀምጣል፦

  • መጠኑን፣ ሰዓቱንና የመጣበትን ባንክ ወይም ዋሌት፤
  • በመልዕክቱ ላይ እንደተጻፈው የላኪውን ስም ወይም የቁጥሩን የመጨረሻ አሃዞች፣ እንዲሁም የማጣቀሻ ቁጥሩን፤
  • የመልዕክቱን ላኪ አድራሻና የመጀመሪያውን ጽሑፍ፤
  • መልዕክቱ ከባንክ መምጣቱ መረጋገጡን።

እርስዎ የሚቆጣጠሩት

  • ማንኛውንም ክፍያ ከዝርዝር ገጹ ላይ ይሰርዙ።
  • ባንኮችንና ዋሌቶችን በማንኛውም ጊዜ በቅንብር ውስጥ ያብሩ ወይም ያጥፉ።
  • የመልዕክት ወይም የማሳወቂያ መዳረሻን በAndroid ቅንብር ውስጥ ያጥፉ፤ ጡሩምባ መልዕክት ማንበብ ያቆማል።
  • ጡሩምባን ሲያራግፉ ያስቀመጠው ሁሉ ይሰረዛል። መተግበሪያው ከAndroid ምትኬ የተገለለ ስለሆነ ሌላ ቦታ ቅጂ አይቀመጥም።

ከስልክዎ የሚወጣው

ምንም። ጡሩምባ ምንም የኢንተርኔት ጥያቄ አያደርግም። መልዕክቶችዎ፣ ክፍያዎችዎና ቅንብሮችዎ ወደ Buna Technologies PLC ወይም ወደ ሌላ ማንም አይላኩም። ድምፆቹ በመተግበሪያው ውስጥ የተካተቱ ቅጂዎች ስለሆኑ ለመናገር ኢንተርኔት አያስፈልገውም።

የመተግበሪያው ጥቅል የAndroidን መደበኛ የኢንተርኔት ፈቃድ ይዟል፤ ጡሩምባ ግን መረጃ ለመላክ አይጠቀምበትም። በአንድ ክፍያ ላይ «መልዕክቱን አጋራ»ን ከነኩ የAndroid የማጋሪያ ዝርዝር ያንን መልዕክት ወደሚመርጡት መተግበሪያ ያስተላልፋል፤ ይህ የሚሆነው እርስዎ ሲነኩት ብቻ ነው።

ፈቃዶች

  • መልዕክት መቀበል፦ ከመረጧቸው ባንኮችና ዋሌቶች የሚመጡ የክፍያ መልዕክቶችን ለማወቅ።
  • የማሳወቂያ መዳረሻ (አማራጭ፣ ከመልዕክት ይልቅ)፦ ለተመሳሳይ ዓላማ።
  • ማሳወቂያ ማሳየት፦ እያንዳንዱን ክፍያና ያልተረጋገጠ መልዕክት ማስጠንቀቂያ ለማሳየት።
  • ከበስተጀርባ መስራት (ከባትሪ ቁጠባ መገለል)፦ ክፍያ ከመግባቱ በፊት Android ጡሩምባን እንዳያቆመው።

ማጋራትና መሸጥ

መረጃዎን አንሸጥም፣ አናከራይም፣ አናጋራም። ከመጀመሪያውም ወደ እኛ አይደርስም።

ልጆች

ጡሩምባ የተሰራው ክፍያ ለሚቀበሉ አዋቂዎች ነው፤ ለልጆች የታሰበ አይደለም።

የዚህ ፖሊሲ ለውጦች

መተግበሪያው መረጃን የሚይዝበት መንገድ ከተቀየረ ለውጡ መተግበሪያው ላይ ከመድረሱ በፊት ይህን ገጽና ከላይ ያለውን ቀን እናሻሽላለን።

አድራሻ

ስለ ግላዊነት ጥያቄ ካለዎት ለBuna Technologies PLC ይጻፉ፦ contact@turumba.et.